46
Downloads
1.2
MB
2007-06-25
መሥራት ለሚችሉ ዜጎች ሁሉ በአገር ውስጥ ምቹ የሥራ ዕድሎች የሚስፋፉበትን ሁኔታ ለመፍጠር መንግሥት የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ውጭ አገር በመሄድ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሠርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል አስፈላጊ በመሆኑ፤ከተቀባይ አገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረም ሕጋዊ የውጭ አገር ሥራ ስምሪትን በማጠናከር ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ጠቃሚ መሆኑ በመታመኑ፤ የግሉ ዘርፍ በውጭ አገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥ ሊኖረው የሚገባውን ተሳትፎ በሕግ መወሰን በማስፈለጉ፤መንግሥት በውጭ አገር ሥራ ስምሪት አፈጻጸም የሚኖረውን የክትትልና የቁጥጥር ሚና ከፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤በሥራ ላይ የነበረውን የሥራና ሠራተኛ ማገናኘት አገልግሎት አዋጅ በአዲስ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ሕግ መተካት አስፈላጊ በመሆኑ፤በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡